የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት ልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ አፀደቀ።

የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት በመደበኛ ጉባዔው በምክር ቤቱ 3ኛ ዙር 11ኛ የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለ ጉባኤ፣ በብሔረሰቦች ምክር ቤት የበጀት አመቱን የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ሪፖርት፣ በምክር ቤቱ የተወሰነ ዓላማን ለማሳካት ስለሚመደብ በጀት እና የክልል መሠረተ

Image
ምክር ቤቱ በ3ኛ ዙር 11ኛ የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔው ልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ በማፅደቅ መደበኛ ጉባዔውን አጠናቋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ብሄረሰቦች ም/ቤት በበጀት ቀመር ዝግጅት እና በሰላም እሴት ግንባታ ዙርያ ለምክር ቤቱ አባላት ስልጠና በወልቂጤ ከተማ ሰቷል ።

ስልጠናውን ያስጀመሩት የምክር ቤቱ ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ አቡቶ አኒቶ የምክር ቤት አባላት በተደጋጋሚ ስልጠና እንዲሰጣቸው እየጠየቁ የቆዩ መሆኑን ጠቅሰው በተመረጡና ከምክር ቤቱ ተግባርና ሀላፊነት ጋር ወሳኝ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልፀዋል ።

Image
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ብሄረሰቦች ም/ቤት በበጀት ቀመር ዝግጅት እና በሰላም እሴት ግንባታ ዙርያ ለምክር ቤቱ አባላት ስልጠና በወልቂጤ ከተማ ሰቷል ።

የዋና አፈ-ጉባዔ መልዕክት

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሄረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ መልዕክት

              አቶ አቡቶ አኒቶ

ሀገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ የተለያዩ ቋንቋዎች፣ ባህሎች፣ ታሪኮች፣ እምነቶች እንዲሁም እምቅ የሆኑ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሀብቶች ባለቤትና የጥንታዊ  ስልጣኔ ባለቤት መሆኗ ይታወቃል፡፡ማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ክልል  ከቀድሞ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ራሱን ችሎ የተደራጀ እና አስር ብሔረሰቦች በጋራ ሆነው  በአንድነት፣ በመፈቃቀድ እና ተስማምተው የመሰረቱት ክልል ነው፡፡ አዲሱ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እጅግ የሚያስደምሙ  ባህሎች፣ ቋንቋዎች፣ ታሪኮች ባላቤት የሆኑ እንዲሁም ታታርና ስራ ወደድ ህዝቦች መኖሪያ ብቻ ሳይሆን በሀገራችን በተለያዩ ክልሎች ከሚገኙ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ጋር ለዘመናት ተቻችለው፣ ተከባብረውና ተፈቃቅረው የሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች  ክልል ነው፡፡  የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በክልሉ ህገ መንግስት አንቀጽ 52 መሰረት በሁለት ምክር ቤቶች ማለትም በክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ብሔረሰቦች ምክር ቤት የተዋቀረው ነው፡፡ የክልላችን ብሔረሰቦች ምክር ቤት በክልሉ ህገ መንግስት አንቀጽ 64 እና የብሔረሰቦች ምክር ቤትን ለማጠናከርና ሥልጣንና ተግባሩን ለመዘርዘር የወጣ አዋጅ አንቀጽ 3መሰረት የክልሉን ሕገ-መንግሥት ይተረጉማል፣ የብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የዞን፤ የልዩ ወረዳ እና የወረዳ አስተዳደር መብት በተመለከተ በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ በሕገ-መንግስቱ መሠረት ይወስናል፤ የክልሉ ሕዝቦች በእኩልነትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ አንድነት እንዲጠናከርና እንዲጎለብት ያደርጋል፤ በክልሉ ውስጥ በሚገኙ አስተዳደር እርከኖች መካከል ለሚነሱ አለመግባባቶች መፍትሔ ያፈላልጋል፤ ውሳኔ ይሰጣል፤በክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ውክልና የሚያስፈልጋቸው ማኅበረሰብ ክፍሎችን በሕግ ይወስናል፤የክልሉ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ታሪክ፣ ባህልና ቋንቋ በሚጎለብትበት ሁኔታ ላይ ይሰራል፤የክልሉ ሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ሃሳብ በማመንጨትና በማሻሻያ ሂደት ይሳተፋል፤ከአጎራባች ክልል መንግስታት ጋር በሚነሱ አለመግባባቶችና የወሰን ማካለል ጥያቄዎች ከክልሎቹ ጋር በጋራ አጥንቶ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያቀርባል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል እንዲሁም የክልሉን የበጀት ቀመር ይወስናል የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ያረጋግጣል፤ ይከታተላል በሚል የተዘርዘሩ  ተግባርና ኃላፊነቶች የተሰጠው ተጨማሪ ያንብቡ

 

የምክር ቤቱ አመራሮች

የተከበሩ አቶ አቡቶ አኒቶ በጅጎ 
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የብሄረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ
የተከበሩ አቶ ገመቹ አረቦ አህመድ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የብሄረሰቦች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ
አቶ ተሾመ ለምጃቦ ሞሎሮ አህመድ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የብሄረሰቦች ምክር ቤት ጽቤት ኃላፊ
ወሮ መድኃኒት ቦጋለ ሶሪ 
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የብ/ም/ቤ/የመ/ኮ/ጉ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር

ብሄር ብሄረሰቦች

 
Image 6Image 3   Image 3Image 2Image 3Image 4Image 5Image 6Image 6    Image 6

News

ምክር ቤቱ በ3ኛ ዙር 11ኛ የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔው ልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ በማፅደቅ መደበኛ ጉባዔውን አጠናቋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት ልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ አፀደቀ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ብሄረሰቦች ም/ቤት በበጀት ቀመር ዝግጅት እና በሰላም እሴት ግንባታ ዙርያ ለምክር ቤቱ አባላት ስልጠና በወልቂጤ ከተማ ሰቷል ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ብሄረሰቦች ም/ቤት በበጀት ቀመር ዝግጅት እና በሰላም እሴት ግንባታ ዙርያ ለምክር ቤቱ…
photo
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ብሄረሰቦች ም/ቤት 3ኛ ዙር 11ኛ የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔዉን በመጋቢት 1/2018…
photo
የፌደሬሽን ምክር ቤት 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በደመቀ መልኩ እንዲጠናቀቅ ለሰሩ ተቋማት ዕውቅና ሰጠ:;
photo
የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ቃል በየም ዞን ሳጃ ከተማ አስተዳደር ህዝባዊ የዉይይት…
photo
መንግስት በሀገሪቱ የሚነሱ የሀሳብ ልዩነቶችን በምክክር መፍታት የሚያስችል ስርዓት ዘርግቷል - አቶ አቡቶ አኒቶ
photo
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት 18ኛዉን የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን አከባበርን አስመልክቶ የዉይይት…
photo
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የብሄረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ አቡቶ አኒቶ የ2017 ዓ/ም…

 ሚዲያ

See More Video

 

ባለድርሻ አካላት

 
Image 6Image 3   Image 3Image 2Image 3

ስለ ብሄረሰቦች ምክር ቤት አስተያየት መስጫ