ዋና አፈ-ጉባዔ
የአፈ-ጉባኤው ሥልጣንና ተግባር፤
አፈ-ጉባኤው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት የኖሩታል፡፡
ምክር ቤቱንና የምክር ቤቱን ጽ/ቤት በበላይነት ይመራል ፤ ያስተዳድራል፡፡
የምክር ቤቱን ስብሰባዎች ይመራል ፣ ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመቀናጀት ዕለታዊ አጀንዳዎችን ይቀርጻል፣ በምክር ቤቱ አባላት እንዲታወቁ ያደርጋል ፣ መደበኛና አስቸኳይ ስብሰባዎችን ይጠራል፡፡
የኮሚቴዎችን ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ ለምክር ቤቱ አቅርቦ ያስመርጣል፡፡
የሕገ-መንግስት ጉዳዮችን አጣሪ ጉባኤ አባላትን ከምክር ቤቱ አባላት መካከል ያስመርጣል፡፡
የጽ/ቤቱን ኃላፊ በክልሉ ህገ-መንግሥት አንቀጽ 64 ንዑስ አንቀጽ 12 መሠረት ለምክር ቤቱ አቅርቦ ያሾማል፡፡
የምክር ቤቱን ቋሚ ኮሚቴዎችና ሌሎች አግባብነት ያላቸው ኮሚቴዎችን ሥራ ያስተባብራል፣ ይከታተላል፡፡
ምክር ቤቱን በመወከል ግንኙነት ያደርጋል፡፡
ከሥልጣንና ተግባራቱ መካከል በከፊል ለምክትል አፈ-ጉባኤው በጽሑፍ ውክልና ሊሰጥ ይችላል፡፡
በውይይት ሂደት የተነሱና ውሳኔ ሊሰጥባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን በመለየት ለድምጽ ያቀርባል፡፡
በዚህ ደንብ በተደነገገው መሠረት የምክር ቤቱን አስተባባሪና ጊዜያዊ ኮሚቴ ያደራጃል ፣ ይመራል፡፡
በሕግ ለአፈ-ጉባኤው ተጠሪ የሆኑ አካላትን ይሾማል፣ ይመድባል፡፡
ምክር ቤቱ በአባሎቹ ላይ የወሰነውን የዲስፒሊን እርምጃ ያስፈጽማል፡፡
የምክር ቤቱን ቋሚ ኮሚቴዎችና የሌሎች አግባብነት ያላቸውን ኮሚቴዎች ሥራቸውን ይከታተላል፡፡
በምክር ቤቱ የሚሰጡትን ሌሎች ተጨማሪ ተግባሮችን ያከናውናል፡፡