የግጭት አፈታት ሠላም ግንባታና ህገ-መንግስታዊ እሴቶች ጥናት ዳይሬክቶሬት
ተልዕኮዉ
በማዕከላዊ ኢትዩጵያ ክልል መንግሥት በሕገ-መንግሥቱ የተቀመጡትን የብሔሮች፣ የብሔረሰቦችና ሕዝቦችን መብቶች መሠረት በማድረግ ብሔረሰቦቹ በየደረጃው ያላቸው ውክልና እና ሌሎች መብቶች ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መከበሩን በማረጋገጥ አለመግባባቶችንና የአለመግባባቶችን መንስኤዎች ዘመናዊና ባህላዊ በሆኑ ዘዴዎች በማጥናትና በመፍታት፣ እንዲሁም የጋራ እሴቶቻቸውን በማጥናትና በማጐልበት በማንነታቸው እንዲኮሩ፣ በእኩልነትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ ዴሞክራሲያዊና ልማታዊ አንድነታቸውን ማጠናከር፡፡