Skip to main content

ስልጤ

የስልጤ ዞን አጠቃላይ ገጽታ

የስልጤ ዞን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት  ከሚገኙ ዞኖች መካከል አንዱ ሲሆን በ10 ወረዳዎች፤ በ5ከተማ አስተዳደር፤ በ168 የገጠርና 67 የከተማ በአጠቃላይ 235 ቀበሌያት የተደራጀ ሆኖ አጠቃላይ የሆነ ቆዳ ስፋት 2537.50 ካሬ ኪ.ሜትር ነው፡፡ የመሬት አቀማመጡ ሜዳ የበዛበት ኘላቶአማ ሆኖ ለእርሻ እና ለእርባታ ምቹ የሆነ አየር ፀባይ ያለው ነው፡፡ ዞኑን በሰሜን ምሥራቅ የጉራጌ ዞን፣ በምዕራብ የሀላባ ዞን፣ በደቡብ ምዕራብ የሀዲያ ዞንና በምሥራቅ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትን ያዋስኑታል፡፡ የዞኑ ዋና ከተማ ወራቤ ከክልሉ ከተማ ከተመሠረተች አጭር ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ያለች ከተማ ነች ወራቤ የማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል የማህበራዊ ክላስተር መቀመጫ ከተማ  ነች ፡፡

 

በ1999 ዓ/ም የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤት መሠረት የዞኑ አጠቃላይ ሕዝብ ብዛት 1,336,018 ነው፡፡ ፕላን እና ልማት ቢሮ 2017 ዓ.ም ፕሮጄክሽን ወንድ 648,965፤ ሴት 687,053 ድምር 1,336,018 እንደሚሆን ይገመታል፡፡ 

በዞኑ በርካታ ድንቅ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶችና መስህቦች ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ጥናትና ቅርስ ጥበቃ የታወቀው የአሳኖ ትክል ድንጋይ ዋነኛው ሲሆን ሌሎችም የትክል ድንጋዮች በአልቾ፤ ወራሮ ወረዳ ቃዋ ቁቶ ጣንዣ ቀበሌ ይገኛል፡፡ የአይናጌ እና የኡርባ ዋሻዎችም እንዲሁ ታሪካዊ ናቸው፡፡ ለሞሮ ፉፍፍሮ፣ ወይራ የተባሉ ፏፏቴዎችና እሹቱ ሙቅ ውሃ፤ የቡራቶ፣ የሀሮ ሻይጣንና ትንሹ አባያ የተባሉ የተፈጥሮ ሐይቆች በዞኑ ሲገኙ ጋሮራ፣ ዌራ፤ ዲጆ የተባሉ ወንዞችና ጋፋት፣ ሙጎ፣ ባለጨኩ ተራራዎችም ጨምሮ በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች ይገኛሉ፡፡ የሀጂ አልዬ ኡምናን፣ አልኪ፣ ጌስቴይ፣ ጣሂራት፥ ገንሠልጢ የተባሉ ጥንታዊ መስጊዶችም ከብሔረሰቡ ታሪካዊ ቅርሶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

የስልጤ ብሔረሰብ

የስልጤ ብሔረሰብ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ውስጥ ከሚገኙ ብሔረሰቦች መካከል አንዱ ነው፡፡ ብሔረሰቡ በዋናነት በክልሉ በስልጤ ዞን ውስጥ በሚገኙ ስምንት ወረዳዎች በሀገር ውስጥ፣ በዎላይታ፣ በሲዳማ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ በሀዋሣ ከተማ እና በሀላባ ዞን  እንዲሁም ከክልሉ ውጪ በጂማ፣ በወለጋ፣ በናዝሬት /አዳማ/ ፣ በሐረር፣ በድሬዳዋ፣ በአዲስ አበባ ከተሞች ከሌሎች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ጋር በስብጥር ይኖራሉ፡፡

የብሔረሰቡ ዋነኛ መኖሪያ ሥፍራ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ በአብዛኛው ሜዳማ ሲሆን የተወስነው በተለይም ምዕራባዊው ክፍል ተራራማነት ያለው ነው፡፡ የአየርንብረቱ በተለያዩ ደረጃዎች ደጋማ፣ ወይናደጋማ እና ቆላማ ሲሆን አብዛኛው ክፍል ወይናደጋማ ነው፡፡ የሕዝቡ ኢኮኖሚ የተመሰረተው በዋናነት በእርሻ ሲሆን ከዚሁ ጎን ለጎን የተወስነው ክፍል የከብት እርባታን፣ ንግድን፣ እና አንዳንድ የእደ ጥበብ ውጤቶችን በማምረት ኑሮአቸውን ይመራሉ፡፡ በዋናነት ከሚመረቱ የእርሻ ምርቶች ጤፍ፣ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ገብስ፣ አቴር፣ ባቄላ፣ ቦሎቄ፣አደንጓሬ፣ ቡና፣ ጫት፣ ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ቋንቋ

የስልጤ ብሔረሰብ አፍ መፍቻ ቋንቋ ስልጢኛ ሲሆን አሴማዊ የቋንቋ ቤተ ይመደባል። ቋንቋው ከአረብኛ፤ ክጉራጊኛ፣ ክሐረሪ፣ ቋንቋዎች ጋር ይመሳሰላል የብሔረሰቡ አባላት ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በተጨማሪ በከተሞች አካባቢ ያለ አማርኛን እንዲሁም እንደ አጎራባችነታቸውና ቅርበታቸው የሀድይ ፣ የማረቆኛ የጉራግኛ፤ የኦሮምፋ እና የሀላብኛን ቋንቋዎች በሁለተኛ ደረጃ ይናገሪ ሉ። ሌሎች አጎራባች ብሔረሰቦች እንዲሁ የስልጢኛን ቋንቋ እንደየቅርበታቸው ለመግባቢያነት ይጠቀማሉ፡፡ ስልጢኛ ከ60 ዓመት በፊት የአረብኛ ፊደልን በመጠቀም ለጽሑፍ የዋ ቋንቋ ቢሆንም ከ1967 ዓ/ም ጀምሮ ልዩ ልዩ አዋጆች እና የመሰረተ ትምህርማስተማሪያ መጽሐፍት የሳባ ፊደልን በመጠቀም በቋንቋው ተተርጉመዋል፡፡ ከ198 ዓ/ም ጀምሮ የ1ኛ ደረጃ የመጀመሪያ ሣይክል የመማሪያ መጽሐፍት በቋንቋው ተዘጋጅተዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የትምህርት ቋንቋ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል እንደዚሁም የሣባ ፊደልን በመጠቀም የመማሪያ መጽሐፍት፣ የስልጢኛ መገ ቃላት፣ የስልጤ ሕዝብ ታሪክ፣ የመረዳዳት ባህል (የስልጤ የአሹራ ባህል)፣ የስል ብሔረሰብ ታሪክ (በክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ) እና ሌሎች መጽሀፍቶች በቋንቋዉ ተጽፈው አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸው ቋንቋው በማደግ ላይ ያለ ስለመሆነ የሚገልፁ እውነታዎች ናቸው፡፡

ታሪካዊ አመጣጥ

የስልጤን ብሔረሰብ ታሪካዊ አመጣጥ በተመለከተ በብሔረሰቡ የዕድሜ ባለፀጋዎ˘ የሚነገሩ ትውፊት እና አንዳንድ የጽሑፍ መረጃዎች የሚሉትን በሁለት መልኩ ከፍለን እንመለከታለን፡፡ የመጀመሪያው የትውፊት መረጃ እንደሚያመለክተው በጥን ጊዜ ዛሬ የብሔረሰቡ አባላት በሚኖሩበት ሥፍራ “ዡራ” ወይንም “ሀርላ” በመባል የሚታወቁ ሕዝቦች ይኖሩ እንደነበር ይገልፃል፡፡ ሌላው መረጃ ደግሞ በ8ኛው ክፍል ዘመን አካባቢ የተወሰኑ ቀደምት የብሔረስቡ አካላት ከምድረ ሣውዲ አረቢያ ተነስተው የኤደን ባህረ ሰላጤን አቋርጠው በስተምስራቅ አቅጣጫ በዘይላ ባህረ-ሰላጤ በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ ያመለክታል፡፡ እነዚህ ሕዝቦች በፀሐይ መውጫ አቅጣጫ ወደ አገሪቱ ክፍል ከገቡ በኋላ በሐረር ጀበርቲ ዛሬ “አደሬ” ወይንም “ሐረሪ በሚባለው አካባቢ ቆይታ አድርገው ወደ ዛሬው መገኛ ሥፍራ በመምጣት ከነባሩ ሕዝብ ጋር ተቀላቅለው መኖር እንደጀመሩ ይነገራል፡፡

የነዚህ ክፍሎች አመጣጥ በአብዛኛው እስልምናን ከማስተማር ጋር የተያያዘ እንደነበርየተገኙ የትውፊት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የተወሰኑ የብሔረስቡ አባላት ደግሞ የግራኝ መሀመድ ወረራ ካበቃ በ1ዐኛው ዓመት ገደማ ከ1553-1563 በሀጂ አልዬ መሪነት በተለያዩ ቦታዎች እየሠፈሩ አሁን በዋናነት ወደ ሚኖሩበት አካባቢ እንደደረሱ ይነገራል፡፡ ሀጂ አልዬ በአባታቸው ኢትዮጵያዊ በእናታቸው የአረብ ዝርያ እንዳላቸው የሚነገር ሲሆን በስፍራው ሲደርሱ በመጀመሪያ መቀመጫቸውን ያደረጉት አልቾ ወሬሮ ላይ እንደነበር በታሪክ ይነገራል። በዚያን ወቅት የነበረው የስልጤ ሕዝብ ወደአሁኑ ስፍራ ከመድረሱ በፊት ገደብ ዝዋይ /ላቂ ደንበል/፣ ሲዳማ፣ አሊቶ ዳገት /ቡልቡላ አጠገብ/ በሚባሉ አካባቢዎች ቆይታ እንዳደረገ የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በወቅቱ ለሕዝቡ እንቅስቃሴ እንደምክንያት የሚገለፀው በግራኝ መሀመድ ወረራ የተነሣና ጥሩ የመኖሪያ አካባቢ ለመፈለግ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በአጠቃላይ በአሁኑ ጊዜ ያለው የስልጤ ብሔረሰብ ከላይ በተገለፀው ሁኔታ በተለያዩ ጊዜያት የመጡ እና የነባር ሕዝቦች የረጅም ዘመን ውህደት ውጤት እንደሆነ ይታመናል፡፡

ባህላዊ አስተዳደር

በስልጤ ብሔረሰብ ውስጥ በርካታ ማህበራዊ ቡድኖች /ጎሣዎች/ ያሉ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ስልጤ፣ መልጋ፣ ችሮ ፣ ዲላባ /ጳ/፣ ኑግሶ /ኦግሶ/፣ አሊቶ፣ አባሮ፣ ኡራጎ፣ ጉምቢ፣ ጊዳዋሁሴንና አለቂሮ ለአብነት ይጠቀሳሉ፡፡ እያንዳንዳቸው በንዑሣን ጐሣዎች የተከፋፈሉ ናቸው፡፡ ከላይ የተገለፁትንም ሆነ ሌሎችንም ጐሣዎች በአንድ ላይ የሚያስተሳስርና የሚያስተዳድር "ጐጐት" የሚባል ባህላዊ አስተዳደር ሥርዓት ያላቸው ሲሆን የሥርዐቱ አፈፃፀም "ሴራ" ወይንም "ዳምቡስ" በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ዓይነቱ ሥርዓት የሚመራው በጐሣ መሪዎች ሲሆን እያንዳንዳቸው የራሳቸው የሆነ የሥልጣን ተዋረድ እና ህጋዊ መተዳደሪያ ደንብ አላቸው።

የብሐረሰቡ ባህላዊ አስተዳደር የተለያዩ የስልጣን ሀላፊነትና የሥራ ድርሻ ያላቸውን አካላት ያቀፈ ሲሆን በዚህ የስልጣን ተዋረድ መሰረት "ገራድ" ዋና ዳኛ ሲሆን ከዚህ በታች ሙሉ ገራድ፣ ወላብግራድ፣ ሣረ ገራድ በመባል የሚታወቁ ረዳቶች አሉት፡፡ ከነዚህ ባህላዊ አስተዳደር አካላት በተጨማሪ የበታች አስተዳደር የሚባሉ "ሞሮ" የጐሣ ተጠሪ፣ ሙራ˚ የአካባቢ ተጠሪና ተላላኪ፣ እና በቤተሰብ ደረጃ የቤተሰብ ሽንጐ የሚባሉ አሉ፡፡ እያንዳንዱ ጐሣ "ሜልቾ" የሚባል ጉባኤ አለው፡፡ ከዚህም ባሻገር እንደየቅደም ተከተላቸው እና የሥራ ተግባራቸው "ማገ" "7" /ህግ ተርጓሚ ፈርዛጎኝ /ይግባኝ ሰሚ ክፍል/ እና ወገጋገኜ በመባል ይጠራሉ፡፡ ይህ ሥርዓት በብሔረሰቡ ውስጥ የሚከሠቱ ግጭቶችንና ወንጀሎችን እንደየክብደታቸው እ ጥፋታቸው መጠን በመመዘን ተገቢውን ቅጣት በመስጠት በባህላዊ መንገድ ግጭት የሚፈታበት አካሄድ አለው፡፡

አንድ የማህበረሰቡ አባል የነፍስ ማጥፋት ወንጀል ቢፈጸም ወንጀሉን አውቆ አስቦበት አሊያም በድንገት የፈፀመ መሆን አለመሆኑን በማጣራትና በመመርመ በባህላዊ መንገድ ፍርድ ይሠጣል፡፡ ይህም በብሔረሰቡ አጋርሳ፣ ተተጋ፤ ሰበባ ተልካና ተልማ በማለት እንደወንጀሎቹ ዓይነት ቅጣት ይቀጣሉ፡፡ በሥርዓቱ "con በሚባል የመሐላ እና የወንጀል ምርመራ ጥበብ ድብቅ ወንጀሎች ይውጣጣሉ: የተጠርጣሪው ወንጀለኛ የወንድና የሴት አያት ወገኖች አብረው መሀላ እንደፈKa ይደረጋል። ይህን ለመፈፀም ፈቃደኛ ካልሆነ ተጠርጣሪው በወንጀለኛነት ይፈረጃል በተለይ የነፍስ ማጥፋት ወንጀል የፈፀመ መሆኑ ከተረጋገጠ የወንጀለኛው ወገኖ; ካሣ ይከፍላሉ፡፡

 

ሴቶች በባህላዊ ሥርዓቱ የመስብሰብ መብት የላቸውም፡፡ በቤተሰብ እና ከአካባቢው ሕዝብ ጋር አለመስማማት ወይም አለመግባባት ሲፈጠር ግን ሴቶች ስሽን‰ "አቤት" ይላሉ፡፡ አቤቱታቸው ተስሚነት ስላለው ፈጣን ምላሽ ያገኛሉ፡፡ በብሔረ ዘንድ የጎሣ መሪው ሚስት “ኢቲኮ” የሚል የማዕረግ ስም ይሠጣታል፡፡ እሱ ሥልጣኑን ሲረከብ ቤተሰቦቿ ከ50-60 ከብቶች በማምጣት ድግስ ደግሠው ለእሷም ለማዕረጓ ተስማሚ የሆነ ዝግጅት ያደርጋሉ፡፡ ሴቶች በኢኮኖሚው እና በሌሎችም ሥራዎች የጎላ ሚና አላቸው:: አብዛኛው ስራ በብሔረሰቡ ሴቶች ጉልበ ይከናወናል፡፡

ባህላዊ እሴቶች

የጋብቻ ሥርዓት

በብሔረሰቡ ዘንድ አምስት የጋብቻ ሥርዓት አይነቶች አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል የመጀመሪያው በስፋት የተለመደው የስምምነት ጋብቻ ነው፡፡ ይህ የጋብቻ አይነት የአግቢው ቤተሰብ ሽማግሌ ወደ ልጅቷ ቤተሰቦች በመላክ በተጋቢዎች ቤተሰ ሥምምነት የሚፈፀም ነው፡፡ ሁለተኛው የጋብቻ ዓይነት "ኩል" ይባላል፡፡ በዚህ የጋብቻ ሥርዓት ልጅቱም ሆነች ቤተሰቦቿ ሣያውቁ አግቢው ፈረስ ላይ ተቀምጦ

ከነፈረሱ በደ ልጅቱ ቤት በመግባት አለንጋዉን በቤቱ ምሰሶ ላይ አስሮ ልጅቱ እንድትሰጠዉ ቤተሰቧን የሚያስገድድበት ነው።

ሶስተኛዉ የጋብቻ ዓይነት ጠለፋ ሲሆን ከወላጅ ከላይ የተጠቀሰዉን እኩል ጋብቻዉን ካልተቀበለ፤ ልጅቱ ወይም ቤተሰቦቿ ልጁን ካልፈለጉ ወይም አግቢው ወጪና 2ጋታን በመፍራት የሚወስደው ሌላ አማራማጅ ነው። በዚህም ልጅቱን ይዞ በመኮብለል በመጨረሻም ሽማግሌ ልክ ጋብቻው የሚፈፀምበት ሥርዓት ነው።አራተኛዉ የጋብቻ ዓይነት ኦጋ የሚባል ሲሆን በዚህ የጋብቻ ስርዓት ሴቷ የመረጠችው ልጅ አባት ቤት ሰተት ብላ በመግባት ምሰሶ ላይ ቅቤ ቀብታ እንዲያገባት የምትጠይቅበት ሥርዓት ነው፡፡ አምስተኛው የጋብቻ ዓይነት የውርስ ጋብቻ የሚባል ሲሆን በዚህ የጋብቻ ሥርዓት ባል ሲሞት የሟች ታላቅ ወይም ታናሽ ወንድም አለያም የቅርብ ዘመድ የሟችን ሚስት የሚያገባበት ወይም የሚወርስበት ሥርዓት ነው፡፡

በብሔረሰቡ ዘንድ ሠርግ እና የጥሎሽ ሥርዓት የሚፈፀመው እንደ ቤተሰቡ ኢኮኖሚ አቅም ነው፡፡ ብር ከሣር ጋር ተጨብጦ ለእናት፣ለአባትና ለቅርብ ዘመዷቿ ጉልበት እየተሳመ ይሰጣል። በስልጤ ብሔረስብ ጋብቻ አፈፃፀም ብዙ ወጪ ያለባቸው የልጅቷ ወገኖች ናቸው፡፡ ለመተዳደሪያ እና ለመቋቋሚያ የሚሆን ቁሳቁስ እና ገንዘብ ቤተስቦቿ ይደጉሟታል፡፡ በቅሎ መውረጃና የመቀነት መፍቻ ተብሎ የልጅቷ አባትና እህቶች ከብት ወይም ገንዘብ ለሙሽሪራዋ ይሸልማሉ። ሠርገኛዉ ወደ ሙሽሪት ቤት ከመሄዱ በፊት “አታካኖ” የሚባል ባህላዊ ምግብ ይመገባሉ፡፡ ልጅቱ ቤት ሠርገኞቹ ቅቤ እንዲጠጡ ይደረጋል፡፡ በሠርጉ ዕለት የሩቅና የቅርብ ዘመድ አዝማድ ይሰበሰባል፤ ከበሮ እየተደለቀ ይዘፈናል፡፡ ሙሽሪትን በቀን ብርሃን ይዞ መውጣት በባህሉ የተከለከለ ነው፡፡ ከጋብቻ በፊት የሴትና የወንድ ልጆች ግርዛት የተለመደ ሲሆን ሴቶች በወሊድ ወቅት ልዩ እንክብካቤ ይደረግላቸዋል።

 

ባህላዊ በዓላት

 

በብሔሰቡ ባህላዊ እና መንፈሳዊ በአላት ይከበራሉ፡፡ አረፋ፣መውሊድ እና ረመዳን ሽዋል" በሚባሉ ወቅቶች ህዝቡ ከበሮ እየደለቀ በዓላቱን ያከብራቸዋል።

ባህላዊ የቤት አሠራር

ብሔረሰቡን የቤት አሠራር ስንመለከት በደጋው የህብረተሰብ ክፍል ጉዬ” የሚባል ትልቅ ቤት በጥድ፣ በባህር ዛፍና በቀርቀህ ይሠራል። በወይናደጋው የሚሰራው ቤት <ጋር> ሲባል መለስተኛ መጠን ያለው ሆኖ በቆላማው ክፍል ደግሞ" ብዙ እንጨትና ሳር የማይፈልጉ የሣር ቤቶች ይሠራሉ፡፡ በነዚህ አካባቢዎች, ሉም ቤቶች ግድግዳቸው በጭቃ ይለሰናል፡፡

የሥልጤ ባህላዊ ቤት ባህላዊ መሣሪያዎች

በዕደ ጥበባት ሥራዎች በኩል ከሸክላ፣ከብረታ ብረት(ማረሻ)፣ከሸማ ስራ አልባሳት አእንጨት ከቀርከሀ እና ክስንደዶ የተለያዩ የመገልገያ ዕቃዎች፣ መጠጫዎችና ጌጣጌጦች፣ የወለል ምጣፎችና የመኝታ ቁሳቁሶች በህዝቡ ዘንድ በግልና በህብረት ይመረታሉ፡፡ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ከሸንበቆ፣ከመቃ እንዲሁም ከብረት የትንፋሽ መሣሪያዎች ከቆዳ ደግሞ ከበሮን በመስራት ለሠርግ፣ ለአመታዊ ባህላዊ በዓላትና ለጭፈራ ይጠቀምባቸዋል፡፡ የጦር መሳሪያዎች እንደጋሻ፣ ጦር፣ ወስፈንጥርእንዲሁም አሽግሌ የተባሉትን በመጠቀም ምርቱን የሚያበላሹባቸውን አውራዎ? ለማጥመድና ለውጊያ ሲገለገልባቸው ኖሯል፡፡

ባህላዊ ምግብና የአመጋገብ ሥርዓት

ብሔረሰቡ በበዓላት ጊዜ የሚያዘጋጃቸው ባህላዊ ምግቦች ሉልሶ (ክትፎ)፣አይብና ጎመን፣የጎመን ክትፎ፣(ጨበሮ) ፣በቅቤ የታሽ ቆሎ (ሀና ቃላ) ይባላል፡፡ እንዲሁም ሻሜታ ይጠጣል፡፡ ቆጮ፣ ጦሮሾና በቆላማ ክፍል ደግሞ እንጀራ በአዘቦት ቀናት ይበላሉ፡፡

ባህላዊ የለቅሶ ስርዓት

ብሔረሰቡ የተለያዩ የለቅሶ ሥርአቶች አሉት፡፡ ትልቅ ሰው ወይም የሀገር ሽማግሌ ሲሞት መልዕክተኛ በተለያየ አቅጣጫ ይላካል፡፡ ፈረሰኛ ከጎረቤት ይመጣል፡፡ ሴቶች እንደየቅርበታቸው መሬት ላይ በመውደቅ ሀዘናቸውን ይገልፃሉ፡፡ የሟች ልብሶች ተይዘው ለቅሶ ይለቀሳል፡፡ ሚች የጎሣ መሪ ከሆነ ከቀብር በኋላ መሪነቱ ለልጅ ይሰጣል፡፡ ወራሹ ህፃን ከሆነ ሞግዚት ይመደብለታል፡፡ ትዳር ሳይመሰርት ለሞተ ሀዘን ይታዘናል።