የዋና አፈ-ጉባዔ መልዕክት

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሄረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ መልዕክት
አቶ አቡቶ አኒቶ
ሀገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ የተለያዩ ቋንቋዎች፣ ባህሎች፣ ታሪኮች፣ እምነቶች እንዲሁም እምቅ የሆኑ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሀብቶች ባለቤትና የጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤት መሆኗ ይታወቃል፡፡ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከቀድሞ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ራሱን ችሎ የተደራጀ እና አስር ብሔረሰቦች በጋራ ሆነው በአንድነት፣ በመፈቃቀድ እና ተስማምተው የመሰረቱት ክልል ነው፡፡ አዲሱ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እጅግ የሚያስደምሙ ባህሎች፣ ቋንቋዎች፣ ታሪኮች ባላቤት የሆኑ እንዲሁም ታታርና ስራ ወደድ ህዝቦች መኖሪያ ብቻ ሳይሆን በሀገራችን በተለያዩ ክልሎች ከሚገኙ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ጋር ለዘመናት ተቻችለው፣ ተከባብረውና ተፈቃቅረው የሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ነው፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በክልሉ ህገ መንግስት አንቀጽ 52 መሰረት በሁለት ምክር ቤቶች ማለትም በክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ብሔረሰቦች ምክር ቤት የተዋቀረው ነው፡፡ የክልላችን ብሔረሰቦች ምክር ቤት በክልሉ ህገ መንግስት አንቀጽ 64 እና የብሔረሰቦች ምክር ቤትን ለማጠናከርና ሥልጣንና ተግባሩን ለመዘርዘር የወጣ አዋጅ አንቀጽ 3መሰረት የክልሉን ሕገ-መንግሥት ይተረጉማል፣ የብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የዞን፤ የልዩ ወረዳ እና የወረዳ አስተዳደር መብት በተመለከተ በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ በሕገ-መንግስቱ መሠረት ይወስናል፤ የክልሉ ሕዝቦች በእኩልነትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ አንድነት እንዲጠናከርና እንዲጎለብት ያደርጋል፤ በክልሉ ውስጥ በሚገኙ አስተዳደር እርከኖች መካከል ለሚነሱ አለመግባባቶች መፍትሔ ያፈላልጋል፤ ውሳኔ ይሰጣል፤በክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ውክልና የሚያስፈልጋቸው ማኅበረሰብ ክፍሎችን በሕግ ይወስናል፤የክልሉ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ታሪክ፣ ባህልና ቋንቋ በሚጎለብትበት ሁኔታ ላይ ይሰራል፤የክልሉ ሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ሃሳብ በማመንጨትና በማሻሻያ ሂደት ይሳተፋል፤ከአጎራባች ክልል መንግስታት ጋር በሚነሱ አለመግባባቶችና የወሰን ማካለል ጥያቄዎች ከክልሎቹ ጋር በጋራ አጥንቶ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያቀርባል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል እንዲሁም የክልሉን የበጀት ቀመር ይወስናል የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ያረጋግጣል፤ ይከታተላል በሚል የተዘርዘሩ ተግባርና ኃላፊነቶች የተሰጠው ተጨማሪ ያንብቡ