Skip to main content

የቢሮው ስልጣንና ተግባር

የብሔረሰቦች ምክር ቤት በዋናነት የክልሉን ሕገ-መንግሥት የመተርጎም፣ የመጠበቅና ሕገ-መንግሥታዊ አሰራሮች አንዲጎለብቱ የማድረግ፣ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሕገ-መንግሥታዊ መብቶቻቸውን በተሟላ መልኩ እንዲጠቀሙ፣ በመካከላቸው የሚከሰቱ አለመግባባቶች በመቻቻልና በአብሮነት መንፈስ መፍትሔ እንዲያገኙና ጠንካራ ክልላዊ አንድነት እንዲጎለብት በማድረግ፣ ካላስፈላጊ የግል ትርክቶች ወጥተን የወል ራዕይ በመሰነቅ የጋራ ጠላት ሆኖ በቆየው ድህነት ላይ የጋራ ክንዳቸውን እንዲያነሱና ወደ ብልጽግና ጎዳና እንዲጓዙ ማስቻል ነው፡፡ በተጨማሪም የክልሉን የበጀት ቀመር መወስን፤ የበጀት ክፍፍል ፍትሀዊነትን፣ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ፣ የመከታተላል ለም/ቤቱ ከተሰጡ ስልጣንና ተግባራት መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ም/ቤቱ በተሰጠው ሕገ-መንግስታዊ ኃላፊነት ዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነትን በማሳደግ ሕብረ-ብሔራዊ ፌደራሊዝምን በማስረጽ የመቻቻል፣ የአብሮነት ባህል መሰረት ያደረገ በዲሞክራሲ ስርዓት የሚመራ እውነተኛ ፌደራሊዝም የማስፈን አቅጣጫ ይከተላል፡፡