Skip to main content

ቀቤና

                                                           የቀቤና ብሔረሰብ
የቀቤና ብሔረሰብ በዋነኛነት በቀቤና ልዩ ወረዳ በሚገኙ በ1 ከተማ አስተዳደር፣ 23 የገጠርና በ1 የከተማ ቀበሌያት ሠፍሮ ይገኛል፡፡ የልዩ ወረዳ ህዝብ ብዛት  2017 ዓ.ም ማ/ኢ/ክ ፕላን እና ልማት ቢሮ ፕሮጄክሽን መሠረት ወንድ 41,947 ሴት 41,814 ድምሩ 83,761 ነው። የተወሰኑ የብሔረሰቡ አባላት ከብሔረሰቡ ዋነኛ መገኛ ውጪ በተለያዩ ቦታዎች ማለትም  በሲዳማ ክልል በበንሣ ወረዳ ፤ በጉራጌ ዞን በአበሽጌ፣ በምሁር አክሊል፣ በእነሞር እና ኤነር እና ማረቆ ወረዳዎች እንዲሁም በሀላባ ልዩ ወረዳ፣ በከምባታ፣ በጠንባሮ ልዩ ወረዳና  እና በሀዲያ ዞኖች ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በስብጥር እንደሚኖሩ የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ብሔረሰቡ የሚገኝበትን አካባቢ በሰሜን የኦሮሚያ ክልል የጐሮ ወረዳ፣ በደቡብ የእዣ እና የቸሀ ወረዳዎች በምዕራብ የአበሽጌ ወረዳ እንዲሁም በምስራቅ የኮኪር እና ምሁር አክሊል ወረዳዎች ያዋስኑታል፡፡
የብሔረሰቡ መገኛ ሥፍራ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ በአብዛኛው ሜዳማ ሲሆን የአየር ንብረቱ በአብዛኛው ወይናደጋ እና ቆላማ ነው፡፡ እርሻና የከብት እርባታ የብሔረበቡ ዋና መተዳደሪያና የኢኮኖሚ መሠረት ሲሆን በዋናነት ጤፍ፣ በቆሎ፣ ሽምብራ፣ ስንዴ ፣ ማሽላ፣ እንሰት፣ ቡና እንዲሁም ከፍራፍሬ ዓይነቶች ብርቱካን፣ አቡካዶ፣ ፓፓዬ እና ሎሚ በብዛት ይመረታሉ፡፡ የብሔሰቡ አባላት ከእርሻው ሥራ ጎን ለጎን የቀንድና የጋማ ከብቶችን ፣ ፍየልና በጐችን ፣ያረባሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የተወሰነው የማህበረሰቡ ክፍል በተለያዩ የእደ ጥበብ ስራ ተሰማርቶ ከሸክላ ከእንጨት እና ከቃጫ የተለያዩ ባህላዊ መገልገያ ቁሳቁሶችን እያመረተ የዕለት ተዕለት ኑሮውን ይመራል።
                                                                             ቋንቋ
የቀቤና ብሔረሰብ የእፍ መፍቻ ቋንቋ ቀቤንኛ ሲሆን ከኩሽ የቋንቋ ቤተሰብ ይመደባል፡፡ ቋንቋው ከሀላቢሳ፤ ከከምባትሣ፣ ከጠንባርሳ እና ከሲዳምኛ ቋንቋዎች ጋርእንደሚቀራረብና አብዛኛው የብሔረሰቡ አባላት፣ ከነዚህ ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝቦች ጋርያለአስተርጓሚ መግባባት እንደሚችሉ ከአካባቢው የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በአጐራባች አካባቢዎች የሚገኙ የብሔረሰቡ አባላት ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በተጨማሪ ጉራግኛንና ኦሮምኛን በሁለተኛ ደረጃ ይናገራሉ፡፡ ቀቤንኛ በአሁኑ ወቅት ክንግግር ቋንቋነት አልፎ የሥራ እና የትምህርት ቋንቋ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል፡፡ ለቋንቋው የጽህፈት አገልግሎት የሣባ ፊደል የተቀረፀለት ሲሆን በዚህም የቀቤንኛ-- አማርኛ መዝገበ ቃላት እና እንደኛ ደረጃ የመጀመሪያ ሣይክል መማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍት በክልሉ ትምህርት ቢሮ አማካይነት ተዘጋጅተው አገልግሎት ላይ ውለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ቋንቋው በአንደኛ ደረጃ ሁለተኛ ሣይክል ትምህርት ቤቶች እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡ ለዚሁም ስራ አጋዥ መሆን የሚችል የቀቤና ቋንቋ ሰዋሰው መጽሐፍ በቀድሙ ክልል በብሔረሰቦች ም/ቤት (2006 ዓ.ም) ተጠንቶና ታትሞ ተሠራጭተዋል።
                                                           ታሪካዊ አመጣጥና አሠፋፈር
ከብሔረሰቡ ትውፊት እና ከአንዳንድ የጽሁፍ መረጃዎች መረዳት እንደተቻለው በሳውዲ አረቢያ እና በየመን መካከል የሚገኘውና “ጠራቢሎስ" የሚባለው አካባቢ ለቀቤና ብሔረሰብ ታሪካዊ አመጣጥ መነሻ እንደሆነ ይነገራል፡፡ የቀቤና ብሔረሰብ ጥንት "ሀዲያ” በሚል ጥቅል ስም ከሚታወቁትና "ገንዝ ገራድ”፣ “ቀቤና ገራድ' እና “አላባ ገራድ” ከሚባሉት ከሦስት ወንድማማች ሕዝቦች ጋር በመሆን ቀይ ባህርን ተሻግረው ጥንት “ጃበርቲ" ተብሎ በሚጠራው በሰሜን ኢትዮጵያ ከኤርትራ እስከ አፋር፣ ከጐጃም እስከ ከስላ ባለው/ አካባቢ መጥተው ለተወሰኑ ዓመታት እንደሠፈሩ፤ ኋላም የሰሜን ኢትዮጵያ ግዛቶችን ይቆጣጠር ከነበረው መንግስት ጋር በግብር አክፋፈል ሥርዓት ምክንያት በተከሰቱ አለመግባባቶች የተነሣ ወደ ደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ በማቅናት ሐረር ውስጥ በ'ጨርጨር አካባቢ ለበርካታ ዓመታት እንደኖሩ ይነገራል። ከዚያም በኋላ ወደ ባሌ ተሻግረው “ሸርካ ገደብ” በሚባል አካባቢ ሰፈሩ። ክሸርካ ገደብ ደግሞ የሲዳማ ብሔረሰብ ወደ ሚኖርበት ሥፍራ በመሄድ እዚያው ረዘም ላሉ ጊዜያት ቆይታ ማድረጋቸውን የሚገልጽ አፈ ታሪክ አላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ የሀዲያ ብሔረሰብ መኖሪያ ወደ ሆነው "ባደዋ መጥተው እንደሠፈሩና እዚያም ለብዙ ዓመታት ቆይታ ማድረጋቸውን የብሔረሰቡ ትውፊት ያስረዳል።
ይሁንና ቀቤናዎች ለራሣቸውና ለከብቶቻቸው የተሻለና የተመቻቸ የመኖሪያ ቦታና የግጦሽ መሬት በመፈለጋቸው ከሲዳማ ወደ ሀዲያ ባደዋቾ፣ከዚያም ወደ " ዋቻ -የዛራው ሆሣዕና፤ ከዋቻሞ ወደ “ሙጐ"በሰባት ቤት ጉራጌና በስልጢ መካከል ያለ ሥፍራ፣ ከሙጐ ወደ “ማፌድ" በመጨረሻም ዘለቄታዊ ጠቀሜታን ወዳስገኘላቸው እና አሁን ወደሚኖርበት አካባቢ በመምጣትና ዝና በነር ላይ በመስፈር የተረጋጋ ኑሮ መኖር እንደጀመሩና ከዚያም ወደ ወልቂጤ አካባቢ መጥተው እንደሰፈሩ ስለ ብሔረሰቡ የተፃፉ መረጃዎችና ትውፊቶች ይናገራሉ፡፡
የቀቤና ብሔረሰብ አሁን ያለበት አካባቢ ደርሶ የተረጋጋ ኑሮ መኖር ከጀመረ በኋላ ማንነቱንና ነፃነቱን የሚፈታተኑ በርካታ ሁኔታዎች አጋጥመውታል፡፡ ለዚህም ከፍተኛ ተጋድሎ አድርጓል፡፡ ከአደረጋቸው ተጋድሎዎች መካከል በግንባርቀደምትነት የሚጠቀሰው በወቅቱ የብሔረሰቡ ጦር መሪ የነበረው ሐሰን እንጃሞ በምኒልክ ጦር ላይ አራት ተደጋጋሚ ድሎችን ማግኘቱ ነው፡፡ ለዚህ ጀግንነቱም ... ሐሰን አንጃሞ የአንበሳ ጥጃ፣ እንኳን ለጐቤ ለንጉስ እንጂ በሚል የስንኝ ቋጠሮ መወደሱም ለዚህ ጥሩ ማረጋገጫ ነው፡፡ ይሁንና ይህ የብሔረስቡ ተጋድሎ በራስ ጐበና ዳጩ በተመራው ጦር ድል በመሆኑ በምኒልክ አስተዳደር ሥር ሊጠቃለል ችሏል፡፡
                                                              ባህላዊ አስተዳደር
የቀቤና ብሔረሰብ “ወማ” በሚል የማዕረግ ስም በሚታወቁ ባህላዊ መሪዎች ይተዳደራል፡፡ “ወማ” ዎች ለሥልጣን የሚበቁት በህዝብ ምርጫና ይሁንታ ብቻ ነው:: በብሔረሰቡ 37 ጐሣዎች የሚገኙ ሲሆን በባህላዊ አስተዳደር ውስጥ Galaxy A35,5Gማ መረጡ 12 ዳኞች ናቸው። ዳኞችም በህዝቡ መካከል የሚነሱ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን የማየት ሥልጣን ያላቸው ሁሉም ሣዎች በሚወአሉበት ግጭቶችን የሚፈቱበት የእስልምና ኃይማኖትንና የብሄረሰቡን ባህላዊ የአስተዳደር irgy mweት በማድረግ ይሆናል። ይህ ባህላዊ ህግ "00% ኦዳ ወይም “ቦበኔ እንዴት እንደተመሠረተ የሚገልፅ ተጨባጭ ማስረጃ ባይገኝም ለ“ቦበኔ”ው መሠረቱ ቅዱስ ቁርአን እንደሆነ ይታመናል፡፡
“ቦበኔ” በብሔረሰቡ መካከል የሚከሰቱ የነፍስ ማጥፋት ወንጀሎችን በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፍላቸዋል፡፡ እነሱም "ሙሉ ያyo" "መዳላ" እና "የመዳላ መዳላ በመባል ይታወቃሉ፡፡ በሁለቱ ደመኛ ወገኖች መካከል ታስቦና ታቅዶ ጭካኒ በተሞላበት ሁኔታ የሚፈፀም ከባድ የግድያ ወንጀል “ሙሉ ደም' ይባላል፡፡ በድንገተኛ አጋጣሚ በሁለቱ ወገኖች መካከል በተፈጠረ ዕለታዊ ግጭት ምክንያት የሚፈፀም የግድያ ወንጀል “መዳላ” ሲባል የመጨረሻውና ዝቅተኛ ደረጃ የተሰጠው የግድያ ወንጀል ደግሞ የመዳላ መዳላ” ይባላል፡፡ ይህም በሁለቱ ወገኖች መካከል ምንም ዓይነት ዕለታዊ ግጭትም ሆነ ቂም ሣይኖር ባልታሰበ አጋጣሚ የሚፈፀሙትንና የነፍስ ማጥፋት ወንጀሎችን ያጠቃልላል።

በማናቸውም መልኩ በብሔረሰቡ የነፍስ ማጥፋት ወንጀል ቢፈፀም ጉዳዩን የሚዳኙት ከሁለቱ ከገዳይም ሆነ አሟች/ ወገኖች ጋር ዝምድና ወይም የደም ትስስር የሌላቸው ገለልተኛ የአገር ሽማግሌዎች ናቸው፡፡ በአጥፊው ወገን ላይ የቅጣት ውሣኔ የሚሰጠውም ባህላዊውን ህግ “ቦበኔ”ን መሠረት በማድረግ ይሆናል፡፡ ግጭቶቹም ወደከፋ ግጭት እንዳያመሩ ለመከላከልና ብሎም ክምንጩ ለማድረቅ ያገርሽማግሌዎች ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋሉ፤ ወዲያው ድርጊቱ እንደተፈፀመ ወደ ሟች ወገኖች በመሄድ የሞተውን ሰው ነፍስ አላህ ለጀነት ያድርገው! ለናንተም አላህ ፅናቱን ይስጣችሁ! ደም ስጡን﷽ ጉዳዩን በሽምግልና ይዘን እንድናየው ፍቀዱልን በማለት ይማፀኗቸዋል። የሽማግሌዎቹ ልመና ከሟች ወገኖች እሺታን እስካላገኘ ድረስ የሟች አስከሬን አይቀበርም፤ ከአዎንታዊ ምላሽ በኋላ ግን አስከሬኑ ይቀበራል፡፡ የገዳይ ወገኖችም ጉዳዩን በያዙት ሽማግሌዎች እጅ ብር 2000 ያስይዛሉ፡፡ ሽማግሌዎቹም ደክመን ሰለቸን ሳይሉ የፀቡን መንስኤ በጥልቀት ማጥናት ይጀምራሉ፡፡ ይህ በሽማግሌዎች የተጀመረው ወንጀልን የማጣራት ተግባርእስከሚጠናቀቅ ድረስ ገዳይና የቅርብ ዘመዶቹ ቀድመው የሚኖሩበትን ቀዬ ለቀው እንዲሄዱ የሟች ወገኖች በሚዘዋወሩበት አካባቢ እንዳይዘዋወሩ በሚገበያዩበት እንዳይገበያዩ በሽማግሌዎች አማካኝነት ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸዋል። የሟች ወገኖችም ቢሆኑ ወደ መደበኛው ፍርድ ቤት ሄደው ክስ እንዳይመሠርቱ ይታዘዛሉ። ይህ ትዕዛዝም “ከተራ” ይባላል፡፡ ይህን የሽማግሌዎችን ትዕዛዝ ተላልፎ የተገኘ ወገን በ "ቦበኔ" ሥርዓትና ህግ መሠረት ይቀጣል፡፡
ቀዬአቸውን ጥለው አንዲሄዱ የተደረጉት ገዳይና የገዳይ የቅርብ ዘመዶች ወደ ትዉልድ ቀዬአቸው እንዲመለሱ የሚፈቀድላቸው "የጉዳገዳይ በሽማግሌዎች ፊት ቀርቦ የእምነት ክህደት ቃሉን የሚሰጥበት የብሔረሰቡ ባህላዊ የወንጀል ምርመራ ሥርዓት ከተፈፀመ በኋላ ነው፡፡ በዚህ የጉዳ ሥርዓት ላይ ገዳይ ቢዋሽ ወይም የተሳሳተ መረጃ ቢሰጥ "በእርሱና በዘር ማንዘሩ ላይ መቅስፍት ይወርዳል" ተብሎ ስለሚታመን ፈፅሞ አይዋሽም፤ ድርጊቱን ከነአፈፃፀሙ አንድ ሳያስቀር ይናዘዛል፡፡
ሽማግሌዎችም ሁሉንም አጣርተው ከመረመሩ በኋላ ለወንጀሉ አፈፃፀም ደረጃ ይሰጡታል፡፡ እንደ ወንጀሉ ዓይነትም የቦበኔን ህግ መሠረት በማድረግ ቅጣት ይወስናሉ፡፡ የተፈፀመወ ወንጀል ከፍተኛ ወይም የሙሉ ደም" ከሆነ ከብር 15 ሺህ እስከ 20 ሺህ ድረስ ገዳዩ ካሣ እንዲከፍል ይደረጋል። ወንጀሉ የ “መደላ" ወንጀል ከሆነ ደግሞ የመጀመሪያውን ግማሽ ብር፤ ዮመደላ መደላ" ከሆነም አንዲሁ የመጀመሪያውን ሲሶ ካሣ እንዲከፍል እንደሚደረግ እና ሁለቱም ወገኖች ደግመው ለፀብ እንዳይፈላለጉ ማሠሪያ ተበጅቶ የእርቁ ሥነ ሥርዓት እንደሚጠናቀቅ የአካባቢው አዛውንቶች ይናገራሉ፡፡ በቀቤና ብሔረሰብ ሴቶች ከፍተኛ ማህበራዊ ቦታ አንዳላቸው ይነገራል፡፡ አብዛኛው የብሔረሰቡ አባላት የእስልምና ኃይማኖት ተከታይበመሆናቸው ሴቶች በኃይማኖት ሥነ-ምግባር ታንፀውና ተኮትኩተው እንዲያድጉ ይደረጋል፡፡
                                                                            ባህላዊ እሴቶች
                                                                            የጋብቻ ሥርዓት
የጋብቻ የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣቶች ለጋብቻ ብቁ መሆናቸው የሚገልፁባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉዋቸው፡፡ ለምሣሌ አንዲት ልጃገረድ ለአቅመ ሔዋን መድረሷን ለማመልከት “ናኦታ ወይም “ጨረር" የተሰኘውን ባህላዊ የፀጉርአስራር ትሠራለች፡፡ የግል ቤትና ንብረት እንዲኖረው መፈለግና ይህም እንዲሟላለት ለወላጆቹ ጥያቄ ማቅረብ ደግሞ ወንዱ ለአቅመ አዳም መድረሱን የሚገለፅበት መንገድ ነው፡፡
በቀቤና ብሔረስብ ሰባት የጋብቻ ዓይነቶች አሉ፤ እነሱም፡- “አጩቁ”- የሚባለውና በወላጆች መልካም ፈቃድ የሚፈፀም ጋብቻ፣ "ጌሡ”- በጠለፋ ወይም በኃይል የሚፈፀም ጋብቻ፣ “ጣጦቄን አዩ”- ድንገቴ የጋብቻ ዓይነት ሲሆን ጋብቻ፣ “ረጋኡ" -የውርስ ጋብቻ፣ “ዶርቱታ”- የምትክ ጋብቻ፣ “ወጌቲታ”- የፈት ጋብቻ፣“ሙሪታ ባዬን አሱ”- የሴቷ ወላጆች ለልጆቻቸው የመረጡላትን ወንድ ጠርተው የሚድሩለት ጋብቻ... ናቸው፡፡
ይሁን እንጂ በብሔረሰቡ ዘንድ በይበልጥ የሚዘወተሩት “አጩቁ” አና “ጣጦቄን አዩን" የተሰኙት የጋብቻ ዓይነቶች ብቻ ናቸው፡፡ የ “አጩቁ” ጋብቻ በወላጆች መልካም ፍቃድ የሚፈፀም የጋብቻ ዓይነት ሲሆን በዚህ የጋብቻ ሂደት ውስጥ ከፍተኛውን ሚና የሚጫወተው የወንዱ ወላጅ አባት አንደሆነ ይነገራል፡፡ አባት ለልጁ የወደፊት ሚስት ትሆንለት ዘንድ ወደመረጣት ልጃገረድ ቤተሰብ አብረውት የሚሄዱትን ሽማግሌዎችን የሚመርጠው እሱ ነው፡፡ ከመረጣቸው ሽማግሌዎች ጋርበመሆን ከልጅቷ ወላጅ አባት ቤት እንደደረሱም “ልጅህን ለልጄ ስጠኝ" የሚል የጋብቻ ጥያቄ የልጁ አባት ያቀርባል፡፡ በብሔረሰቡ የቆየ ልማድ መሠረት ለዚህ ዓይነቱ የጋብቻ ጥያቄ “አልሰጥም!” የሚል ቀጥተኛ ምላሽ ወዲያው መስጠትም ሆነ በማናቸውም መንገድ ጥያቄውን ይዘው የመጡትን ሽማግሌዎች አሳፍሮ መመለስ እንደፀያፍ ተግባር ይቆጠራል፡፡ ይህም ማለት ግን ለጥያቄው ሁሌም አዎንታዊ ምላሽ ይሰጣል፤ የጠየቀ ሁሉ ያገባል ማለት አይደለም፡፡
በቀጥታ አይሁን እንጂ ለሽማግሌዎች አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ምላሽ በተዘዋዋሪ የሚስጥባቸውና በብሔረሰቡ የተለመዱ በርካታ መንገዶች አሉ፤ አጭር ወይም ረዥም ቀጠሮ መስጠት ዋነኛው ስልት ነው፡፡ የልጅቷ አባት በጉዳዩ ላይ ተማክሮ መልስ ለመስጠት ለሽማግሌዎቹ አጭር /ከሁለት ሣምንት ያልበለጠ/ ቀጠሮ ከሰጠ ጋብቻውን የፈቀደ ወይም በጋብቻው የተስማማ መሆኑን፤ ረዥም እስከ ሦስት ወር የሚቆይ ቀጠሮ ከሰጠ ደግሞ ጋብቻውን ያልፈቀደ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከሁለት ሣምንት ያልበለጠ ቀጠሮ የሚሰጣቸው ሽማግሌዎችም በቀጣዩ ቀጠሮ ሌሎች ሽማግሌዎችን ጨምረው ጫትና ስኳር ይዘው ወደ ልጅቷ ወላጅ አባት ቤት ይመለሳሉ፡፡ እንደተጠበቀውም ከልጅቷ ወላጆች "ልጃችንን አላህ ከሰጣችሁ እኛም ለልጃችሁ ሰጥተናል" በማለት መስማማታቸውን ይገልፃሉ፡፡ ይህ የይሁንታ ምላሽ አንደተሰማም ኮርማ በሬ ታርዶ ይበላል፣ የኒካ” /ቀለበት/ ሥርዓትም ይፈፀማል። አንዲት የቀቤና ልጃገረድ “ኒካ” ከታሠረላት በኋላ ሌላ ማንም ወንድ አይደፍራትም፣ ትከበራለች፣ ትታፈራለችም፡፡ በሆነ አጋጣሚ በሌላ ወንድ ብትጠለፍ ወይም ብትደፈር ጠላፊው በ"በቦኔ” ህግ መሠረት ይቀጣል፡፡ ለድርጊቱም “አቂድ” /ካሣ/በብሔረሰቡ መንፈሳዊ መሪዎች አማካይነት ሁለቱም ወገኖች በቃላቸው ለመፅናት “ስጥቻለሁ” “ተቀብያለሁ" በማለት ቃል ኪዳን የሚገቡበት የቃል ኪዳን ሥርዓት ነው፡፡ ጠላፊው _ ወይም ደፋሪው ካሳ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ የካሣው መጠንም በአማካይ ከ1500-2ዐዐዐ ብር እንደሚደርስ ይገመታል።
ሌላው በብሔረሰቡ የሚዘወተረው የጋብቻ ዓይነት “ጣጦቄን አዩ” የሚሰኘው የድንገቴ ጋብቻ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ጋብቻ አንዳንዴ “ተጠምጥሞ ገባ” በሚል ስያሜውም ይታወቃል፡፡ አግቢው ወጣት ከጓደኞቹ ጋር በመሆን ሣይታሰብ በድንገት ከወደዳት ልጅ ወላጆች ቤት ገብቶ “አልወጣም” በማለቱ ምክንያት የሚፈፀም ጋብቻ በመሆኑ ነው "ተጠምጥሞ ገባ” መባሉ፡፡ ይህ ዓይነቱ ጋብቻ ለልጅቱ ወላጆች ዱብዕዳ /ድንገተኛ/ ይሁን እንጂ ለተጋቢዎች ግን ድንገተኛ አይደለም፡፡

በሁለቱ ተጋቢዎች መካከል ቀደም ሲል በሚስጢር የተስማሙበት ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ዓይነት ከነጓደኞቹ የገባው ወጣት ከየት አንደመጣ? ምን እንደሚፈልግ? ቤታቸውንም ለቆ እንዲወጣ በልጅቷ ወላጆች ቢጠየቅም አይወጣም፤ ቤታቸውን የሙጥኝ ይላል፡፡ ከልጅቱ ወላጆች የይሁንታን ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ ከገባበት ቤት ንቅንቅ አይልም፡፡ ልጅቷም ፍቅረኛዋ “ተጠምጥሞ መግባቱን ስታውቅ ወዲያው በቅርብ ጓደኞቹ ትታጀባለች፣ አፍታም ሣይቆዩ የልጁ ወላጆች ልጃቸው ካለበት ከልጅቷ ወላጆች ቤት ሽማግሌ ይልካሉ፡፡ በዚህ መልኩ ጉዳዩ በሽምግልና ያልቅና ልጅቷ ትሞሸራለች። በተሞሸረች በአንድ ሁለት ቀን ውስጥም ጋብቻው ይፈፀማል፡፡ የጥሎሽ ሥርዓትም በዚሁ ዕለት ይከናወናል፡፡ የሚሰጠው የጥሎሽ ዓይነትና መጠን እንደሰጪው የመስጠት አቅም ይወሰናል፡፡ ክብት፣ ብር እና የተለያዩ አልባሳት ይሰጣሉ፡፡ ሆኖም ግን ይህ የጥሎሽ መጠን መናር በርካታ ወጣቶች ክጋብቻ እንዲርቁና እንዲሸሹ በማድረጉ ምክንያት የጥሎሹ መጠን ወደ 150 ብር ዝቅእንዲል በባህላዊ የአስተዳደር ጉባኤ ተወስኗል ።
ነፍሰ-ጡር የሆነች የቀቤና ሴት ልትወልድ አንድ ወይም ሁለት ወር ሲቀራት አይብ እንዲሁም ክትፎ ከጐመንና ከስጋ/ አዘጋጅታ ጐረቤቶቿንና የቅርብ ዘመዶቿን ትጋብዛቸዋለች፡፡ ተጋባዦችም በአፀፋው በሠላም አንድትገላገል ይፀልዩላታል፡፡ ይህ ዓይነቱ ሥርዓትም "ጀበፍተሡ" ይባላል፡፡ እንዲሁም አሁን ቀረ እንጂ ጥንት አንዲት አራስ ሴት ከአራስ ቤት እስከምትወጣ ድረስ ወላጅ እናቷ ክትፎ አዘጋጅታ ከቤቷ ድረስ የምታመጣላት “መገንቤሱታ" የሚባል ባህላዊ ሥርዓት ሁሉ እንደነበረ የአካባቢው አዛውንቶች ያስታውሳሉ፡፡
                                                                               ባህላዊ
                                                                    ባህላዊ የቤት አሠራር
ብሔረሰቡ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተለያየ መጠን ያላቸውን የሣር ቤቶች ይሠራል። ትልቅ የሣር ቤት ለቤተሰቡ መኖሪያነት ትናንሽ “ሐለዋ"/ የሚባሉ የጐጆ ቤቶችን ደግሞ ለእንግዳ መቀበያነት ያዘጋጃል፡፡ በአንድ አካባቢ አንድ ትልቅ መስጊድ በጋራ አማካይ በሆነ ሥፍራ ላይ ሠርተው በጋራ እንደሚጠቀሙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ እንዲሁም ብሔረሰቡ የተለያዩ የእርሻ መሣሪያዎችንና የቤት መገልገያ ቁሣቁሶችን ራሱ አዘጋጅቶ ይገለገልባቸዋል፡፡ ከጠንካራ እንጨት፣ ጫፉ ሹል ተደርጐ የሚዘጋጀውና “ዜጌዛ በመባል የሚታወቀው የእርሻ መሣሪያ ለዚህ ተጠቃሽ ነው፡፡ "በርኩማ /የሴቶች መደገፊያ/፣ “ዳለጌ” /መቀመጫ/ ና “ኮቤ” /ነጠላ ጫማ/ ብሔረስቡ ከእንጨት የሚያዘጋጃቸው የመገልገያ መሣሪያዎች ናቸው፡፡ ከቆዳ -ለወንዶች ትራስ፣ ከቀንድ- የክትፎ መብያ ማንኪያ፣ ከሸክላ “ዋዲያት” /ትልቅ የክትፎ ማዘጋጃ ከብሔረሰቡ የዕደ ጥበብ ውጤቶች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ባህላዊ በዓላትን በተመለከተ በቀቤና ብሔረሰብ ከተለመዱት መንፈሳዊ በዓላት ውጭይህ ነው የሚባል ባህላዊ በዓል የለውም። የሚያከብራቸው በዓላትም በእስልምና ኃይማኖት ዘንድ የታወቁትን በዓላት ብቻ ነው፡፡ “የቀሳሌ" የብሔረሰቡ ባህላዊ ጨዋታ ነው። ቀጭንና ልምጭ እንጨት በመወርወር ይከወናል፡፡ ትግል የከፍታ ዝላይ፣ ግልቢያ 'ገሌተ አለዳ/፣ ሩጫ ሌሎች የብሔረሰቡ ባህላዊ ጨዋታዎች ናቸው ።
                                              ባህላዊ የአመጋገብ ሥርዓት
ገንፎ፣ የቡላ እንኩሮ እና የቆጮ ድፎ በሥጋ በቀቤና ብሔረሰብ ዘንድ ከሚዘወተሩት ባህላዊ ምግቦች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ጥንት “ሠርጉ ፊታ" የሚባልና ከገብስ የሚዘጋጅ ባህላዊ መጠጥም ብሔረሰቡ ያዘጋጅ እንደነበር ከልዩ ወረዳው  የተገኙ ምንጮች ያመለክታሉ፡፡
                                         ባህላዊ የአለባበስ ሥርዓት
ከጥጥ የሚዘጋጅ የሽመና ውጤቶችን መልበስ በቀቤናዎች ዘንድ የተለመደ ባህላዊ አለባበስ እንደሆነ የዕድሜ ባለፀጋዎች ይናገራሉ፡፡ አዛውንቶች ከጥጥ የተሠራ ነጭሱሪና ሽሚዝ ወገባቸው ላይ ይለብሳሉ፡፡ ሴቶች ከታች ቡልኮ በመቀነት ታጥቀው ከላይ ጥብቆ ይለብሳሉ፡፡ ፀጉራቸውን በነጭ ሻሽ እጃቸውን በአንባር ያስጌጣሉ፡፡ እንዲሁም ወጣቶች ደግሞ ከታች ሰፊ ቁምጣ ከላይ ደግሞ ጥብቆ መልበስ ያዘወትራሉ፡፡
                                                   የለቅሶ ሥርዓት
የብሔረሰቡ የሀዘንና የለቅሶ ሥርዓት ክእስልምና ኃይማኖት ሥርዓተ-ህግ /ከሼሪያ ህግ/ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በመሆኑም አንድ ሰው ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ የተጋነነ ለቅሶም ሆነ ሀዘን እምብዛም አይስተዋልም። የኃይማኖት መሪዎች ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ በመጀመሪያ ዮጆና ኢዛል” /የስግደት/ ሥርዓት ይከናወናል፡፡ ከዚያም “ላኢላህ-ላኢላላህ…” እየተባለ አስከሬኑ ወደ ቀብሩ ቦታ ከተወሰደ በኋላ ግብአተ-መሬቱ ይፈፀማል፡፡