የዋና አፈ-ጉባዔ መልዕክት

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሄረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ
አቶ አቡቶ አኒቶ
ሀገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ የተለያዩ ቋንቋዎች፣ ባህሎች፣ ታሪኮች፣ እምነቶች እንዲሁም እምቅ የሆኑ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሀብቶች ባለቤትና የጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤት መሆኗ ይታወቃል፡፡ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከቀድሞ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ራሱን ችሎ የተደራጀ እና አስር ብሔረሰቦች በጋራ ሆነው በአንድነት፣ በመፈቃቀድ እና ተስማምተው የመሰረቱት ክልል ነው፡፡ አዲሱ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እጅግ የሚያስደምሙ ባህሎች፣ ቋንቋዎች፣ ታሪኮች ባላቤት የሆኑ እንዲሁም ታታርና ስራ ወደድ ህዝቦች መኖሪያ ብቻ ሳይሆን በሀገራችን በተለያዩ ክልሎች ከሚገኙ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ጋር ለዘመናት ተቻችለው፣ ተከባብረውና ተፈቃቅረው የሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ነው፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በክልሉ ህገ መንግስት አንቀጽ 52 መሰረት በሁለት ምክር ቤቶች ማለትም በክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ብሔረሰቦች ምክር ቤት የተዋቀረው ነው፡፡ የክልላችን ብሔረሰቦች ምክር ቤት በክልሉ ህገ መንግስት አንቀጽ 64 እና የብሔረሰቦች ምክር ቤትን ለማጠናከርና ሥልጣንና ተግባሩን ለመዘርዘር የወጣ አዋጅ አንቀጽ 3መሰረት የክልሉን ሕገ-መንግሥት ይተረጉማል፣ የብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የዞን፤ የልዩ ወረዳ እና የወረዳ አስተዳደር መብት በተመለከተ በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ በሕገ-መንግስቱ መሠረት ይወስናል፤ የክልሉ ሕዝቦች በእኩልነትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ አንድነት እንዲጠናከርና እንዲጎለብት ያደርጋል፤ በክልሉ ውስጥ በሚገኙ አስተዳደር እርከኖች መካከል ለሚነሱ አለመግባባቶች መፍትሔ ያፈላልጋል፤ ውሳኔ ይሰጣል፤በክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ውክልና የሚያስፈልጋቸው ማኅበረሰብ ክፍሎችን በሕግ ይወስናል፤የክልሉ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ታሪክ፣ ባህልና ቋንቋ በሚጎለብትበት ሁኔታ ላይ ይሰራል፤የክልሉ ሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ሃሳብ በማመንጨትና በማሻሻያ ሂደት ይሳተፋል፤ከአጎራባች ክልል መንግስታት ጋር በሚነሱ አለመግባባቶችና የወሰን ማካለል ጥያቄዎች ከክልሎቹ ጋር በጋራ አጥንቶ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያቀርባል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል እንዲሁም የክልሉን የበጀት ቀመር ይወስናል የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ያረጋግጣል፤ ይከታተላል በሚል የተዘርዘሩ ተግባርና ኃላፊነቶች የተሰጠው ም/ቤት ነው፡፡
በመሆኑም ም/ቤቱ የክልሉን ሕገ-መንግሥት የመተርጎም፣የመጠበቅና ሕገ-መንግሥታዊ አሰራሮች አንዲጎለብቱ የማድረግ፣የፌዴራሊዝምና የህገመንግስት አስተምሮ ለኅብረተሰቡ ተደራሽ የማድረግ፤ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሕገ-መንግሥታዊ መብቶቻቸውን በተሟላ መልኩ እንዲጠቀሙ፣ በመካከላቸው የሚከሰቱ አለመግባባቶች በመቻቻልና በአብሮነት መንፈስ መፍትሔ እንዲያገኙና ጠንካራ ክልላዊ አንድነት እንዲጎለብት የማድረግ፣ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ፣ የመከታተላል፤ በብሔር ማንነትና በአገራዊ ማንነትን ሚዛናዊነት በጠበቀ መልኩ አገራዊ ትርክት ላይ በመመሰረት የጋራ ጠላት ሆኖ በቆየው ድህነት ላይ የጋራ ክንዳቸውን እንዲያነሱና ወደ ብልጽግና ጎዳና እንዲጓዙ የማስቻል ኃለፊነቶችን ይወጠል፡፡
በዚህም መሰረት ምክር ቤቱ በመተግበር ላይ ያለውን ሕገ-መንግሥታዊ ኃላፊነቶቹን አጠናክሮ ለመቀጠል የሚረዱ የተለያዩ ተግባራቶችን ያካተተ ዓመታዊ ዕቅድ ለማስጽደቅና ለመገምግም ም/ቤቱ በአመቱ ሁለት ጊዜ ጉባኤ የሚያኖረው ሲሆን ለም/ቤቱ የውሰኔ ሀሳቦችን የሚያቀርቡና ለም/ቤቱ ተጠሪ የሆኑ እያደንደቸው አምስት አባላት ያሉት ሶስት ቋሚ ኮሚቴዎች ማለትም የሕግ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ፣ የብሔረሰቦች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ እና የበጀት ድልድል (የቀመር) ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ተደራጅቷል፡፡ በተጨማሪም በህግ መንግስት አንቀጽ 82 እና የክልሉ ህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አባላትን ለማደረጀት የወጠው አዋጅ አንቀጽ 4 መሰረት በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የሚመራ አሰራ አንድ አባላት ያሉት ህግ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አባላት ተድራጅተው የህገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ ሲቀርብ ለም/ቤቱ ውሳኔ ሀሰብ ለማቅረብ በሚያስችል መልኩ ተደራጅቷል፡፡
ም/ቤቱ በዋናናት የሚመረበት የህግ ማዕቀፎች የኢፌዴሪ ህገ መንግስት፤ የማዕካላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህገ መንግስት፤የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የብሔረሰቦች ምክር ቤትን ለማጠናከርና ሥልጣንና ተግባሩን ለመዘርዘር የወጣ አዋጅ፤የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የብሔረሰቦች ምክር ቤት የአሠራርና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ፣የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አዋጅ እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያለቸው ህጎች ናቸው፡፡
በአጠቃላይ ም/ቤቱ በተሰጠው ሕገ-መንግስታዊ ኃላፊነት ብሔረሰባዊና አገራዊ ማንነት በሚመለከት ሚዛን የሚጠብቅ፤ ሕብረ-ብሔራዊ ፌደራሊዝምን በማስረጽ የመቻቻል፣ የአብሮነት ባህል መሰረት ያደረገ በዲሞክራሲ ስርዓት የሚመራ እውነተኛ ፌደራሊዝም የማስፈን አቅጣጫ ይከተላል፡፡ ይህን አቅጣጫ በመከተል ም/ቤቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ተግባራቶች በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡